.png)
AFG Gospel Band
1996 - 2003
AFG (All For God, All From God) was a popular gospel band in Ethiopia between 1996 and 2003. It was the first group of its kind, blending gospel and reggae music into popular acapella songs. The founding members of this innovative group were Berissa Lemessa, Biniam Beyene, Motuma Sima, Shewangizaw Abera, and Yonas Gorfe. The group later expanded, welcoming four instrumentalists and a female vocalist: Daniel Shiferaw on bass guitar, Gideon Tadesse on keyboards, Mekonnen GebreMariam on drums, Yewondwossen Bisrat on guitar, and Wesene (Sherry) Tadese as vocalist.
AFG wrote many of their own songs (in Amharic, English and Afan Oromo). They recorded two albums, a cassette tape in around 1999 entitled AFG Gospel Band and a CD in 2003 entitled The Gospel According to Reggae.
AFG performed regularly in churches around Addis Ababa, particularly for special youth programs, and always had a huge turnout. They traveled twice to Scandinavia and once to US of America to perform in churches and varies mission gatherings. The group dissolved in 2003.
ኤ.ኤፍ.ጂ
1988 - 1995
ኤ.ኤፍ.ጂ- AFG (All For God, All From God) በጣም ታዋቂና ተወዳጅ የመዘምራን ቡድን ነበር። ባንዱ ከ1988 ዓ.ም እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ አብሮ የዘለቀ ነበር። ባንዱ ሲጀምር በአምስት አባላት በአካፔላ አዘማመር ሲሆን ጀማሪዎቹም ሞቱማ በዳሳ፣ ቢኒያም በየነ፣ ሸውንግዛው አበራ፣ በሪሳ ለሜሳ እና ዮናስ ጎርፌ ነበሩ። በኃላ አካፔላ ይዘቱን ሳይለቅ ባንዱ የሬጌ ዘይቤን በማካተት አራት ሙዚቀኞችና አንድ ሴት ድምጻዊት ጨመረ። እነሱም መኮንን ገ/ማርያም (ድራም)፣ ዳንኤል ሽፍራው (ቤዝ ጊታር)፣ የወንዶሰን ብስራት (ሊድ ጊታር)፣ ጌዲዮን ታደሰ (ኪቦርድ) እና ወሰኔ (ሼሪ) ታደሰ (ድምጻዊ)።
ኤ.ኤፍ.ጂ የራሱን ኦሪጂናል መዝሙሮችን በተለያዩ ቋንቋዎች የምጽፍ ሲሆን አነዳንዴም የታወቁ መዝሙሮችን እንደገና በማቀናበር ይዘምር ነበር። ባንዱ አብሮ በነበረበት ጊዜ ሁለት አልበሞች ያስቀረጸ ሲሆን አንደኛው በ1991 ዓ.ም ሲሆን ሁለተኛው በ1995 ዓ.ም ነው።
ኤ.ኤፍ.ጂ በአዲስ አበባና በተለያዩ የሐገራቱ ቦታዎች በመዘዋወር የመዝሙር አገልግሎት ሲሰጥ የነበረና በተለይ የወጣቶች ፕሮግራም ላይና እንዲሁም አለም አቀፍ ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት ዝማሬዎቹን አቅርቧል። ሁለት ጊዜ ወደ እስካንዴኔቪያ ሐገራት የተጓዘ ሲሆን አንድ ጊዜ ደጎሞ ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዟል። ቡዱኑ በ1995 ተበትኗል።






