.png)
Books / መጽሐፍ
ፕሮቴስታንታውያን በኢትዮጵያ ፖለቲካ
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የምናየው ሚስዮናውያኑ እምነታቸውን (ንጹሕ ወንጌልን፤ በእነሱ አባባል) ለሀገሬው ሕዝብ ለማስተማርና ተከታይ ለማፍራት፣ ከዘመኑ የፖለቲካ ሰዎች ጋራ የተጫወቱትን የፖለቲካ ጨዋታና በኋላ ደግሞ የሀገሬው አማንያን ከሚስዮናውያኑ ተረክበው እምነቱን ሲያስፋፉ፣ በየጊዜው ከነበሩት የፖለቲካ መሪዎች ጋራ ያደረጉትን መልካምም ኾነ አስቸጋሪ ጕዞ የሚቃኝ ነው፡፡
የመጽሐፉ ርእስ በቀጥታ እንዳሳየው፣ የመጽሐፉ ማገርና መዋቅር የተሠራው ፕሮቴስታንታውያን በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት የፖለቲካ ውቅር ውስጥ የነበራቸውን ሚና የሚዳስስ ነው። ‹ፕሮቴስታንታውያን› የሚለው ቃል በራሱ በጣም አሻሚ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ የበለጠ የተዘበራረቀ ትርጓሜ ያለው ነው።
ከዐፄ ፋሲለደስ (1632) እስከ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (2010-20..)
መጽሐፉ
ጀፋር መጽሐፍ መደብር.....ለገሐር ከኖክ ነዳጅ ማደያ አጠገብ ወይም አራት ኪሎ ከብርሀነ ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
መካነ ኢየሱስ መጽሐፍ መደብር....መካኒሳ
ኢማና መጽሐፍ መደብር...ቦሌ ጌቱ ኮመርሻል 1ኛ ፎቅ
Protestant Involvement in Ethiopian Politics
In Protestant Involvement in Ethiopian Politics, Yonas Gorfe offers a compelling exploration of the complex and often turbulent relationship between Protestant faith and political power in Ethiopia. Tracing the journey from early missionary efforts to the modern-day ambitions of local church leaders, Yonas uncovers the delicate political manoeuvres foreign missionaries had to employ to spread what they called the "pure gospel."

A Historical Review from the time of King Fasilides (1632) to Prime Minister Dr. Abiy Ahmed (2018-20..)
Kindle version is available for pre-order. The paperback will be available on May 28, 2025.
ቤት ያጣው ቤተኛ
ሙዙቃ፣ሙዙቀኛነትእናኢትዮጵያዊቷቤተክርስቲያን
ይህ መጽሐፍ የስሜት ውጥረት መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገፍቶ ተገፍቶ መድረሻ ያጣው ሙዚቀኛ የጩኸት ድምጽ ነው። ይህ መጽሐፍ “አሁንስ የፓስተሮቹና የመሪዎቹ የግብዝነትና ያላዋቂነት መጠን ልኩን ዐልፏልና ‘በቃ’!!” ብሎ የሚጮኽ ድምጽ ነው። ይህ መጽሐፍ ሙዚቀኛው ስለ ራሱ የሚናገርበት መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ “እኔ ሙዚቃ እንደ ማንኛውም ሙያ (አነጢነት ይሁን ዶክተርነት፣ ጋዜጠኛነት ይሁን ፖለቲከኛነት) በማቀርበው ሥነ ምግባር ልገምግም እንጂ በደፈናው መወገሬ ይብቃ” የሚል የሲቃ ጩኸት የምታሰማበት የሙዚቃ የራሷ ድምጽ ነው። ይህ መጽሐፍ የተቀናጣ የሥነ መለኮት ክርክር አይደለም፥ የመኖር (survival) እና የሕይወት ጥያቄ እንጂ። በአጠቃላይ ይህ መጽሐፍ በስሜት የተሞላ የነጻነት ድምጽ ነው።
The 3rd edition is available in select book stores in Addis Ababa, Ethiopia and through mail order around the world. The 1st edition is available on Amazon.
The Controversy of Zefen and Mezmur
This book discusses the controversy of zefen (secular music) and mezmur (spiritual music) in the Protestant Church in Ethiopia. Owing to the inappropriate translation of Galatians 5: 19-22, in which the Amharic Bible deviates from any other translation (including the Greek), the musician in the Ethiopian Protestant Church is painted as a professional destined for eternal doom.

Order from Amazon. Available in paperback and Kindle.